የአዲስ አባበ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መረሐ ግብሮች ያስተማራቸው ከ9ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

የአዲስ አባበ ዩኒቨርስቲ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሸመ እና የተለያዩ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በ2010 ዓ.ም በተለያዩ መረሐ ግብሮች ያስተማራቸው ከ9ሺ700በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታ፣ በርቀትና በክረምት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን 9 ሺህ 724  ተማሪዎችን አሁን በሚሊኒየም አዳራሽ በማስመረቅ ላይ ነው፡፡

ከተማራቂዎቹ መካከልም 2 ሺህ 746 ሴት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ  6 ሺህ 44 በቅድመ ምረቃ፣ 3 ሺህ 407 ደግሞ በድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን 273ቱ በሶስተኛ ዲግሪ የሚመረቁ ናቸው።

የወርቅ ሜዳሊያ ከሚሸለሙ 12 ተመራቂዎች መካከል ሰባቱ ሴቶች ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደማይሰጥ መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡

በአጠቃላይ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ዓመት 170 ሺህ 578 ተማሪዎችን የሚያስመርቁ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 32 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡