በኢትዮጵያ በተለያዩ ግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች የተመድ የ15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

ባለፉት ጊዚያት በኢትየጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች የተመድ የ15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መልቀቁን አስታውቋል።

ድርጅቱ ባወጣው መረጃ መሰረት የገንዘብ ድጋፉ ከ36 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አስቸኳይ የአልሚ ምግብ እርዳታ፣ 600 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች አስቸኳይ የውኃ አቅርቦት፣ ለ71 ሺህ 200 ለሚሆኑ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍና ለ175 ሺህ ዜጎች ደግሞ የጤና አገልግሎት ይውላል ተብሏል።

የድርጅቱ ማከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ፈንድ በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል፤ የአስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ነው መልቀቁን ያስታወቀው።

የገንዘብ ድጋፉም አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹት እነዚህ ተፈናቃዮች የሚውል ነውም ተብሏል።(ኤፍቢሲ)