የማህበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎትን በመላው ሀገሪቱ ወጤታማ በሆነ መልኩ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው- የጤና ጥበቃ ሚኒስትር

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎትን በመላው ሀገሪቱ ወጤታማ በሆነ መልኩ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ተናገሩ

ሚኒስትሩ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደገለጹት የዛሬ 10 አመት በጥቂት ወረዳዎች የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና ስራ በአሁኑ ጊዜ በ511 ወረዳዎች ተግባራዊ መሆን ችሏል፡፡

የተሻሉ ተሞክሮዎች እየተቀመሩ በመላው ሀገሪቱ እንዲተገበር ስራዎቹ በቅንጅት እየተካወኑ ነውም ብለዋል

በአዲስ አበባ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና ስራው ውጤታማ ሲሆን  በተለይ በልደታ ከፍለ ከተማ በዘርፉ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛ ነውም ተብሏል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በቡኩላቸው ይህን ስራ ለማሳለጥ የበለጠ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋ ይሠራል ነው ያሉት፡፡