ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን አነጋገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን በፅህፈት ቤታቸው ጠርተው አነጋግረዋል፡፡

ኮሚቴዋቹ በእርቅና ሰላም ረገድ አርዓያ መሆን እንዳለባቸው የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር የቤቴክርስቲያኒቱ ሰላም መሆን የሀገር ሰላም መሆን እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ሳምንት በአሜሪካ በሚኖራቸው ቆይታ ለሰላም የሚከፈልን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል ቤተክርስቲያንቷ ወደ ሰላም እንዲትመለስ ጥረት እንዲያደርጉ አስራ አንድ አባላትን ለያዘው አሸማጋይ ኮሚቴ አደራ ብለዋል፡፡

የእርቀ ሰላሙ ጉዞ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደደረሰና በሁለቱም በኩል ያሉትን አባቶች በማስማማት በቅርቡ የሰላም እና የፍቅር ብስራት በኢትዮጵያ እንደሚሆን የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያም ሆነ በአሜሪካ የሚገኙት የሀይማኖት አባቶች ላደረጉላቸው ቀና ትብብርና ለሰጧቸው መልካም ምላሽ የኮሚቴው አባላት አመስግነዋል፡፡

አስራ አንዱ የአሸማጋይ ኮሚቴ አባላት በቀጣዩ ሳምንት ወደ አሜሪካ በሚጓዙበት ወቅት የእርቅ ሂደቱን እንደሚቋጩ እና በአሜሪካ የሚገኘውን ሲኖዶስ ወደ አገር ቤት ይዘው እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው