ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተወጣጡ የማዕረግ ተመራቂዎች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጎበኙ

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተወጣጡ የማዕረግ ተመራቂዎች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ጎብኝተዋል፡፡

ከ400 በላይ የሚሆኑ የማዕረግ ተመራቂዎች ፋርላማን የጎበኙ ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አሰራሮች ዙሪያ ገለፃ ተደርጎላቿል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌ ጉባኤ ወይዘሮ ሙፌሪያት ካሚል ወጣቶች ፋርላማውን መጎብኘታቸው ትልቅ እድል እንደሆነ አንስተው ለቀጣይ ተማሪዎችም ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ከማዕረግ ተመራቂዎች ጋር በነበረው ውይይት ተማሪዎች በአንዳንድ ቦታ እየተፈጠሩ ባሉ የሰላም ችግሮች ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፌጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለጥያቂያቸው ምላሽ የሰጡ ሲሆን በምላሻቸው በየጊዜው ችግሮችን ለመፍታት ባለመሰራቱ ዜጎች ለሞትና ሌሎች ኪሳራ እዲጋለጥ ተደርገዋል ብለዋል፡፡

የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙት ህገ-መንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ በመሆኑ የዜጎች ሞትና መፈናቀልን መከላከል ይገባዋል ነው ያሉት፡፡

ተመራቂዎቹ በሌሎች ጉዳዮች ላይም ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡