የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂዎች የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኙ

በዘንድሮ ዓመት የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂዎች የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

ለተመራቂ ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለት በሀገሪቱ ስለሚገኙ የኢንዱስሪ ፓርኮች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

ተመራቂዎቹም በተደረገላቸው ገለፃ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ባዩት ነገር መደሰታቸውንና በቀጣይ በሀገሪቱ ላይ ለሚኖራቸው አበርክቶ መነቃቃትን እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት የማዕረግ ተመራቂዎች የተለያዩ ከፍተኛ ተቋማትን እንደጎበኙ ገልጸው በተመረቁበት ዘርፍ ሀገሪቱ የጀመረችውን ለውጥ ለማስቀጠል የበኩላቸውን እንደሚወጡ እና ለውጡን  ለማስቀጠልም እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡

ከ400 የሚበልጡ እነዚህ ተመራቂዎች ከፍተኛ የሆነ ተስፋ የተጣለባቸው ሲሆን በጉብኝታቸው ወቅት ብዙ ልምዶችን እንደቀሰሙ ገልጸዋል፡፡

አሁን እየተደረገላቸው ያለው ውይይት በትምህርት ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ትልቅ መነቃቃት እንደምፈጥርላቸውም ጠቁመዋል፡፡