የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሲኖዶስ ችግሮች መፈታታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ችግሮች ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፈታታቸው ተግልጿል።

በሀገረ ውስጥና ከሀገር ውጭ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሶች መካከል የተከሰተው ችግር ለባለፉት 26 ዓመታት የዘለቀ ሲሆን፥ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች ተደርገው ሳይሳካ መቆቱ ተገልጿል።

የሁለቱን ሲኖዶሶች ችግር ለመፍታት ባለፉት ሶስት ዓመታት በተለይም ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባለፉት ሶስት ወራት ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው።

በዚህም ዛሬ በዋሽንግተን በተካሄደው የሁለቱ ሲኖዶስ መድረክ ችግሩ መፈታቱ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መካከል የነበረው ችግር ዛሬ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት አግኝቷል ተብሏል።

በአሜሪካ ዋሽምግተን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባልደረባ አቶ አብርሃም ሃይሌ ያነጋገራቸው የሃይማኖት አባቶችና ኢትዮጵያዊያን የዛሬን ቀን ለረጅም ዓመታት ሲመኙት የቆየ መሆኑን ተናግረዋል።

የሃይማኖት አባቶች ችግር በመፈታቱም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸውም አስተያየት ሰጭዎቹ ያስረዳሉ።

ስምምነቱ የሀይማኖት አባቶች የሌሎችን ችግር ለመፍታት ያስችላቸዋል ተብሏል።(ኤፍቢሲ)