ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ከተለያዩ አገራት የስፔስ ሳይንስ ተመራማሪዎችና ተማሪዎችን አነጋገሩ

የኢፌዴሪ ፕሪዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የስፒስ ሳይንስ ተመራማሪዎችን እና ተማሪዎችን አነጋግረዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ከቻይና ፣ከህንድ ከአሜሪካና ከኢትየጵያ የተውጣጡ ናቸው፡፡መቀመጫውን ሎስአንጀለስ ካሊፎርኒ ያያደረገው ዋስል የተሰኝው አለምአቀፍ ድርጅት ከኢትዮጵያ ስፒስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በጋራ በመሆን ዘርፉን ለማሳደግ ተማሪዎቹ የተለያዩ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ስፒስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ሁለት ኢትዮጵያዊ ወጣቶችን ለሶስት ሳምንት ያክል በአሜሪካ ስልጠና እንዲወስዱም በማድረግ ላይ ነው፡፡በተመሳሳይ በሚቀጥለው አመት ስምንት ኢትዮጵያዊን ወጣቶችን ስልጠና እንዲወስዱ ያደርጋልም ተብሏል፡፡

የኢፌድሪ ፕሪዝዳንት ደ/ር ሙላቱ ተሾመም ድርጅቱ ከኢትዪጵያ ስፒስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ለሰራው ስራ ለማበረታታት እና የወጣቶች ተሳትፎ እንዲያድግ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡