በጌድኦና ጉጂ ዞኖች ያሉ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰብ ተሣትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

በጌድኦ እና ጉጂ ዞኖች ያሉ ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰብ ተሣትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከርን አላማው ያደረገ የሰላም ኮንፌረንስ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ አጎራባች በሆነው ሚጪጫ ቀበሌ ተካሂደዋል፡፡

በኮንፌረንሱ ላይ የተገኙት የጌዴኦ እና ጉጂ አባገዳዎች እርቀ ሰላም መካሄዱን ተከትሎ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው የቀድሞ ኑሯቸውን እንዲጀምሩ ህዝብን ከህዝብ ማቀራረብ  የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ደህንነታቸው እንዲጠበቅ የባህል ሽማግሌዎች ከሚያከናወኑት ሠላ የማስፈን ስራ በተጓዳኝ መንግስት ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል የህግ በላይነትን ማረጋገጥ መቻል እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡

ዘለላቂ ሠላም በአካባቢው እንዳይወርድ የሚንቀሳቀሱ አካላትን በመለየት እና የተጀመረው ህዝቦች የማቀራረብ ተግባር ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ሰው የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ እርቀ ሰላን ወደ ህዝብ በማውረድ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር መንግስት የጀመራቸውን የህግ በላይነት የማረጋገጥና ሠላማዊ ቀጠና የመፍጠር ስራን ውጤታማ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡

ዞጎችን ወደ ቀየያቸው ለማስመለስ የወደመ ሃብት ንብረቶችን የመተካት ተግባር በመከናወን ላይ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈናቃዮችን የመመለሱ ተግባር እንደሚጀመርም ገልጸዋል፡፡

የምዕራብ ጉጂ ዞን ወና አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቦኖ በበኩላቸው አሁን ባሉ ነባራዊ ሁኔታ በዞኑ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ተከትሎ በአጎራባች አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ወደ ቀያቸውተመልሰው በመኖር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በውስጥም የዜጎችን የስራና የኑሮ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ሲሆኑ የአካባቢው ህብረተሰብም ለሚመለሱ ሰዎች ያላቸውን እያካፈለ ይገኛል ብለዋል፡፡ (ምንጭ፤ የጌዴኦ ዞን መ/ከ/ጉ/ጽ/ ቤት)