አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደአገሩ እንዲመለስ ጥሪ ቀረበለት

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ያደርግ የነበረውን አስተዋጽዎ እንዲቀጥል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ አቅርበውለታል፡፡

በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁለቱ ፌዴሬሽኖች ለአትሌት ፈይሳ የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እኤአ 2016 በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ሀገሩን ወክሎ በማራቶን በተካሄደው ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል፡፡