በሊቢያ ለተሰውት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ ማዕከል ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ

ሚያዝያ 11፣ 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ለተሰውት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አጽም ማረፊያ እና የመታሰቢያ ማዕከል መገንባት መጀመሯን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሲቲያን አስታወቀች፡፡

የቤተክርስቲያኗ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊና የቅዱስ ፓትሪያርኩ ረዳት ሊጳጳስ ዶክተር ብጹዕ አቡነ አረጋዊ እንደተናገሩት በማዕከሉ አዳራሽና የመታሰቢያ ሐውልትም ይገነባል፡፡

በተጨማሪም በየዓመቱ ሚያዚያ 11 ኢትዮጵያውያኑ የሚዘከሩበት ቀን እንዲሆን ቤተክርቲያኗ መወሰኗንም አክለው ገልጸዋል፡፡

መታሰቢያ ማዕከሉ ለትውልዶች ከሚያስተላልፈው የእምነት ጽናት ባሻገር አፍሪካ ህብረት ፊት ለፈት በሚገኘው ደብረምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴደራል ቤተክርስቲያን ውስጥ መገንባቱ በአካባቢው በርካታ አህጉራዊና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች የሚገኙበት በመሆኑ ድጊቱን ለማውገዝና የህገወጥ ስደትን አስከፊነት ለማስተማር ይሆናል ተብሏል፡፡