ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትምህርት ዘርፍ ሁሉን አቀፍና አካታች ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ገለጹ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትምህርቱ ዘርፍ ሁሉን አቀፍና አካታች ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የተጀመረውን ሃገር አቀፍ የትምህርት ፖሊሲ ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ፎረምን በንግግር ከፍተዋል።

ዘርፉ የተፈለገውን ግብ ለማሳካት ሁሉን አቀፍና አካታች ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አስፈረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ዘርፉን የተሻለና ውጤታማ ለማድረግ ማሻሻያው እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።

ከዚህ ባለፈም በቴክኖሎጅ የታገዘ አሰራር መከተል እንደሚገባም አንስተዋል።

ዛሬ በተጀመረው ፎረም እስከ ፈረንጆቹ 2030 ባለው የትምህርት ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን ለአምስት ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል።

በውይይቱ ላይም ከ26 ዘርፎች የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡