ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆች ድጋፍ አደረጉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆች ለሆኑ 200 ተማሪዎች ዛሬ የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ለገሱ።

ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር  ፅህፈት ቤት በተከናወነ ስነ ስርዓት ነው ድጋፉ የተበረከተው።

ዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ህፃናት ድህነትና ችግር በእውቀታቸው በማሸነፍ ጠንካራ መሆን እንደሚጠበቅባቸው

ህፃናት ጠንካራና የተሻለ ደረጃ ሲደርሱ ለሌሎች ትልቅ ተስፋ እንዲሁም ደጋፊ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ድህነትና ችግር ህፃናትን ከያዙ አለማ ሊያደናቅባቸው እንደማይገባ ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እርሳቸው ያለፉበትን መንገድ በምስሌነት በማንሳት ለተማሪዎቹ አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው ህፃናትንና የአረጋውያን ቤቶች የማደስና የመደገፍ ልምድ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ባለሀብቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ወጣቶች እና ሌሎች አቅም ያላቸው የህብተሰብ ክፍሎች በዚህ አይነት በጎ ተግባር በመሳተፍ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዲናዋ በበጎ ፈቃደኞች ድጋፍ እየተደረገላቸው ካሉት ነዋሪዎች መካከል የሆኑትን እማሆይ አዱኛን በቤታቸው ተገኝተው ጎብኝተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር  ፅህፈት ቤት ሀላፊ ከአቶ ፍፁም አረጋ የትዊተር ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎች ድጋፍን ለሚሹ ወገኖች በመድረሱ  እንዲሁ ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊ እና ደጋፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ለዚህም አርዓያ ለመሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በመዲናዋ በበጎ ፈቃደኞች ቤታቸው የታደሰላቸውን ዜጎች ጎብኝተዋል።(ኤፍቢሲ)