ታግዶ የነበረው ህጋዊ የውጭ አገራት የሥራ ስምሪት በመስከረም ወር መጨረሻ ይጀምራል

ለአመታት ታግዶ የነበረው ህጋዊ የውጭ አገራት የስራ ስምሪት በ2011 ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ እንደሚጀመር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ዳይሪክተር ጀነራል አቶ ብርሃኑ አበራ እንደገለፁት ስምሪቱ እስካሁን የዘገየው ስምሪት ከሚደረግባቸው አገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ማድረግ አስፈላጊ ስለነበረ ነው፡፡

የዜጎችን ደህንነትና ክብር ለማስጠበቅ ከተቀባይ አገራት ጋር የሚደረገው ስምምነት ወሳኝ መሆኑንም ነው አቶ ብርሃኑ የገለፁት፡፡

ህጋዊ የስራ ስምሪትን ለማሳለጥ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባሻገር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡

አዋጁ በ2008 ዓ.ም ቢፀድቅም እስከ አሁን ተግባራዊ ሳይሆን እንደቆየ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ የዜጎችን የስራ ስምሪት አስመልክቶ ከሳኡዲ አረቢያ፣ ካታር እና ጆርዳን ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በመደረጉ የስራ ስምሪቱ በ2011 ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ ዳይሪክተር ጀነራሉ ገልፀዋል፡፡