ጉባኤው ከኃይማኖት አባቶች ጋር መከረ

የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት ከኃይማኖት ተቋማት ከተወጣጡ ኃይማኖት አባቶች ጋር መከረ፡፡

ጥላቻን በማስወገድ ይቅርታን ማድረግ፣ ፍቅርን ማብዛት፣ ያለንን ማካፈል፣ አንድነትን፣ ሠላምን እና መከባበርን ማጠናከር የሚል መሪ ቃልን የያዘው የምክክር መድረኩ የኃይማኖት ተቋማት የተፈጠረውን ሀገራዊ መግባባት በማቀናጀት በቀጣይም የኃይማኖት ተቋማት ሊሰሩ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

የኃይማኖት ተቋማት እስከዛሬ የነበረውን የኢትዮጵያዊያን እሴቶች አስጠብቆ በማስቀጠል ከነሐሴ 28/ 2010 ዓ.ም ጀምሮ የበጎ ተግባራት ስራዎችን ባህል ሆኖ እንዲቀጥል መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በአዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ መልካም እሴቶች ከምን ጊዜውም በላይ እንዲጠናከሩና የዘመቻ ስራ እንዳይሆኑ የኃይማኖት ተቋማት ሊሰሩ ይገባልም ተብለዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት የተወከሉ የሃይማኖት አባቶች መሳተፋቸው ተገልጸዋል፡፡