የኢትዮጵያ ቄራዎች ድርጅት የአዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ቄራዎች ድርጅት መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል አስመልክቶ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ህገወጥ እርድ የሚያስከትለውን  ዘርፈ ብዙ ችግር አውቆ ከድርጊቱ እንዲታቀብም ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡

ከዚህም ባሻገር ጤንነቱ የተረጋገጠ እርድን ለማከናወን ይቻል ዘንድ በድርጅቱ ውስጥ ለሚሰሩ ከ1ሺ 2 መቶ በላይ ሰራተኞቹ በገዳይነቱ የሚታወቀውንና ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውን ሄፓታይተስ ቢ የተሰኘውን የጉበት በሽታ ለመከላከልም  በከፍተኛ ወጪ ክትባት እየሰጠ መሆኑንም ገልጿል፡፡