በካርቶን የታሸገ 3 ሚሊየን 5መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61 ሺህ 400 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የክትትልና ኦፐሬሽን ዲቪዚዮን አባላት ለክፍሉ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ከሁለት የውጭ ሀገር ዜጎችና ከአንድ ኢትዮጵያዊ በህገ ወጥ መንገድ በካርቶን ሊዘዋወር የነበረ 3 ሚሊዮን 5መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብርና 61 ሺህ 4መቶ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

አባላቱ ከሦስቱ ተጠርጣሪዎች የቀረበላቸውን ሁለት ሚሊየን ብር መደለያ በመቃወም ተጠርጣሪዎቹን ከእነ ኤግዚቢቱ ለህግ አቅርበዋል፡፡ 

የኮሚሽኑ አባላት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በልዩ ልዩ አጋጣሚ የሚቀርብላቸውን መደለያ በመቃወም ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለህግ እያቀረቡ እንደሚገኙና እነዚህን መሰል መልካም ተግባራት ሊበረታቱና ዕውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡ (ምንጭ: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)