በአዲስ አበባ አማርኛና አፋን ኦሮሞን አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ እንደሚጠቀም ቢሮው አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማርኛና አፋን ኦሮሞን በመንግስት ትምህርት ቤቶች አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ እንደሚጠቀም ገለፀ።

የቢሮዉ ሃላፊ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን በሰጡት መግለጫ የ2011 የትምህርት ዘመን በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል።

 ቢሮው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በየደረጃዉ እንዲከናወኑ ያደረገ መሆኑን እና ቅድመ ዝግጅት ያላደረጉ ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለማስወገድና የመምህራንን ጥቅማ ጥቅምችን በማስጠበቅ ረገድም በተያዘዉ ዓመት ሰፊ ስራዎች ይሰራሉ ነው ያሉት።

የትምህርት ማህበረሰብ ለትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራት፣ ተገቢነት እና ፍትሃዊነት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል።

አፋን ኦሮሞ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር እንደየተማሪዉ የመማር ፍላጎት መጠን በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች አማራጭ የትምህርት መስጫ ቋንቋ አድርጎ እንደሚጠቀም አስታውቀዋል።

የመምህራንና የትምህርት አመራሮች እውቅና መርሃ ግብር መስከረም 19 በኢትዮጵያ የባህል ማዕከል ይካሄዳል። (ምንጭ: የቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት )