የመጀመሪያው የኢሬቻ የሰላም ሽልማት ተካሄደ

የመጀመሪያው ኢሬቻ የሰላም ሽልማት ስነ ስርዓት በትናንትናው እለት ተካሂዷል።

የኢሬቻ የሰላም ሽልማት በብሄራዊ የባህል የተካሄደ ሲሆን፥ ሀገሪቱ ሰላም እንድትሆን የተጉ ኢትዮጵያውያን ባለውለታዎች የመጀመሪያው የኢሬቻ የሰላም ሸልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚህም መሰረት፦

• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪኮች ብጹዕ ወቅዱስ ማቲያስ
እና ብጹዕ ወቅዱስ መርቆሪዮስ

• አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ

• ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሐጂ ኡመር እድሪስ

• የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች የመጀመሪያው የኢሬቻ የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።
• የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌ ገራድ ኩልሚዮ መሀመድ ገራድ

በኪነ ጥበብ ዘርፍ

• ጽምጻዊ አሊ ቢራ

• ድምጻዊ መሃሙድ አህመድ እና

• አርቲስት ለማ ጉያ የኢሬቻ የሰላም ሽልማት ተሸላሚ መሆን ችለዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)