የኢረቻ በዓል በቢሸፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ በድምቀት ተከበረ

ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ በትናንትናው  እለት ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝብ በተገኘበት  በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓልኢሬቻ ለፍቅርና ለአንድነትበሚል መሪ ቃል ነው በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ በተባለው ሥፍራ  በድምቀት  ተከብሯል። 

በበዓሉ ላይም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች፣ ከውጭ ሀገራት የመጡ ዳያስፖራዎች እና በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቷል ።

ሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች፣ የጋሞ ብሔረሰብ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ የሀዲያ እና የኮንሶን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮችም በበዓሉ ላይ ታድመዋል።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ደማቅ በሆነ ስነ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል።

ኢሬቻ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት መገለጫ ከሆኑት ወስጥ አንዱ ሲሆን፥ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች በስፋት የሚከበር የባህልና እሴት መገለጫ የምስጋና በዓል ነው።