ማህበሩ በአገሪቷ የተለያዩ ክፍሎች ለተፈናቀሉት ዜጎች የ40 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ለተፈናቀሉትና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጥቂት ወራት ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች ለጉዳት ለተዳረጉት እና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሠረታዊ ድጋፎችን ማድረጉን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በደቡብ፣ በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ እና አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈለግቻው ዜጎች ነው መሰረታዊ ደግፎችን ማድረጉን ያስታወቀው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን የሚያስፈልጋቸውን ሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የአቅም ውስንንት እያጋጠመው መሆኑን ያስታወቀው፡፡

ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ባለው አቅም እየደገፈ ቢሆንም በሚደረግላቸው ድጋፍን በተመለከተ የሚቀርበው ቅሬታ መረጃው እንደለለው ገልፀዋል፡፡