የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከ2 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ሰጠ

በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከ2 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የእድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች መነሻ ገንዘብ እንዲቆጥቡ በማድረግ  ለእያንዳንዳቸው  140 ካሬ ሜትር ቦታ ነው የሰጣቸው፡፡

ቦታውንም በማህበራት እንዲደራጁ ከተደረገ በኋላ በእጣ እንዲከፋፈሉ ነው የተደረገው፡፡

የእድሉ ተጠቃሚዎች ቦታውን በህገወጥ መንገድ  ወደ ሶስተኛ ወገን ማዘዋወር እንዳይችሉ የሚያደርጉ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

የቤት መስሪያ ቦታ ያገኙ ሰዎችም ቦታውን ለሌላ አሳልፈው እንደማይሰጡና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መኖሪያ ቤታቸውን እንደሚያስገነቡ ለዋልታ ቴሌቪዥን አስረድተዋል፡፡

የክልሉ መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር  ቢሮ  በበኩሉ በክልሉ ቤትና ንብረት የሌላቸው፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች  እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች በእድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጿል፡፡