የጎዴ አጠቃላይ ሆስፒታልና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ ሊደረግላቸው ነው

የጎዴ አጠቃላይ ሆስፒታልና የከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ ሊደረግላቸው ነው።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሞሃመድ ኡመር ለማስፋፊያ ግንባታዎቹ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ ስኪያጅ ዶክተር መሃመድ ሻፊ፥ የፕሮጀክቱ የሆስፒታሉ አቅም እንደሚያሳግ እና እስከ 2 ሚሊየን የሚጠጉ የከተማዋን እና አጎራባች ወረዳ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የሁለቱ ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ወጪ የማስፋፋያ ፕሮጀክቶቹ ዲዛይን ሲጠናቀቅ እንደሚታወቅም ተገልጿል።

ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፋ ሞሃመድ ኡመር ከስዓት በዋላ ከአዳዲሌ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር በመልካም አስተዳደር እና በሌሎች ጉዳይች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም በክልሉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚንቀሳቀሱ የገለፁት ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ፥ ህዝቡም ከጎናቸው እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላለፈዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)