ኢትዮ-ቴሌኮም በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የተሰበሰበውን ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለሜቄዶንያ አስረከበ

ኢትዮ-ቴሌኮም በአጭር ጽሑፍ መልዕክት የተሰበሰበውን ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አስረከበ፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም ገንዘቡን ለማዕከሉ ገቢ ማድረጉን ለደንበኞች በላከው የአጭር ጽሑፍ መልዕክት አስታውቋል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት ለማዕከሉ 74 ሚሊየን 718 ሺህ 165 ብር በአጭር ጽሁፍ መልዕክት መሰብሰብ መቻሉ  ሜቄደንያ  ለሚያካሄደው  የበጎ ተግባር ሥራ  ትልቅ እገዛ  ይኖረዋል ተብሎ  ይጠበቃል ።

ከአንድ ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ማዕከሉን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

በጉብኝቱ ላይም ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው 15 ዘመናዊ ዊልቸር ለማዕከሉ አበርክተዋል፡፡