ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰው የሚለውን ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰው የሚለውን ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡

ውድድሩ በሰባት የተለያዩ ምድቦች የተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከተሰጠው ድምፅ ከ85 በመቶ በላይ በማግኘት የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚለውን ሽልማት አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡

በእንግሊዝ የሚታተመው የአፍሪካ ሊደርሺፕ መፅሔት ነው የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰው የሚለውን ሽልማት አሸናፊ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን መሆናቸውን ያበሰረው፡፡ (ኢዜአ)