የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ

የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር ከመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርጓል፡፡

በምክክራቸውም መከላከያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚያስገነባውን የሃይ ፕርፎርማንስ ኮምፒውቲንግ ሲስተምን መጠቀም እንዲችልና በምርምር ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ መከላከያን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያርግና በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ለጤና እና ለግብርና ዘርፍ ለተለያዩ ግልጋሎቶች ሀገር ውስጥ ገብተው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ኬሚካሎች ማስወገድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሃመድ  የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ አመራሮች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

አመራሮቹ የኢኖቬሽና ቴክሎጂ ሚኒስቴርን የጎበኙ ሲሆን የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ዋና ዋና የስራ እንቅስቃሴዎችን የተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ (ምንጭ፡-የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)