ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመላው አገሪቱ ከተውጣጡ 3 ሺህ 696 መምህራን ጋር እየተወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ ከ3 ሺህ 696 መምህራን ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ከመምህራን ጋር ቀጣይነት ያለውን ውይይት ማድረግ የመጪውን ትውልድ የመገንባት በተለይም አዲሱን የትምህርት ፍኖተ ካርታ ለመተግበር ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

መጪው ትውልድ አገሩን ለማገልገል እንዲተጋ ማስቻልና ማሳወቅ መምህራን ለአገር ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም መምህራን ዋርካ ናቸው በማለት ያለባቸውን የከለላ ኃላፊነት አውስተዋል፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)