የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላ ሃገሪቱ በድምቀት ተከበረ

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (ገና) በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሃገሪቱ በድምቀት ተከብሯል። 

በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት ተከብሮ ውሏል።      

በተለይም በላል ይበላ ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በማከናወን በድምቀት መከበሩን  ተገልጿል።

በርካታ የእምነቱ ተከታዮችም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በማህሌት እና ቅዳሴናሌሎች ሥርቶችን በማካሄድ  ሌሊቱን አሳልፈዋል።

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል  ከዘጠኙ ዐብይ በዓላት ውስጥ አንዱ ነው።       

የኃይማኖት መሪዎች በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የክርስትና እምነት ተከታዮች ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር በመተባበር ለሀገር ሰላም በተጠናከረ መልኩ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፥ ለእምነቱ ተከታዮችም ሁሉም ለሀገር አንድነት እና ሰላም መትጋት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተለያዩ የኃይማኖት መሪዎችም በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ በተፈጠሩ ችግሮች ዙሪያም መንግስት በጀመረውና ሀገራዊ አንድነት እና ሰላምን ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ሁሉንም ማሳተፍ እንዳለበት ጠቁመዋል።