የወራቤ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዙር ተማሪዎቹን ተቀበለ

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 500  የ2ኛ ዙር ተማሪዎቹን ተቀብሏል፡፡

ለተማሪዎቹ ከወራቤ ከተማ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ተማሪዎች በቆይታቸው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ  እነዚህ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም ወራቤ የፍቅር እና የመከባበር ከተማ እንደሆነች ጠቁመው ይህንን አኩሪ ባህል ለማስቀጠል በማለም ተማሪዎቹን እስከመንገድ ድረስ በመውጣት መቀበላቸውንም አስረድተዋል፡፡

ተማሪዎችም በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ዩኒቨርሲቲው ሳይጠራቸው በመዘግየቱ ግን ቅር ተሰኝተው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶክተር መሃመድ አወል በበኩላቸው ጥሪው የዘገየው ዩኒቨርሲቲው አዲስ እንደመሆኑ የመሰረተ ልማት ችግሮች ስላሉበት እንደሆነ ገልጸው አሁንም የመሰረተ ልማት ችግሮቹ ሙሉ በሙሉ እስኪቀረፉ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል ፡፡