የጥምቀት በዓል በዛሬው እለት በመላ ሀገሪቱ ተከብሯል

የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በዛሬው እለት በመላ ሀገሪቱ ተከብሯል፡፡

በዓሉ በአዲስ አበባ ሲከበር ተገኝተው መልዕክት ያስለተላለፉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ዕለቱ መከባበርና አንድነት እንዲሁም ይቀርታን በማድረግ ሊከበር ይገባዋል ብለዋል፡፡

በዚህ ዕለትም ወጣቱ ባህሉን ጠብቆ ለቀሪው ትውልድ እንዲተላለፍ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በዚህ ረገድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርም እየሰራ መሆኑን ነው ተናግረዋል፡፡