ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ በውጭ ፖሊሲ ምርጥ ውጤት ካስመዘገቡ 10 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በውጭ ፖሊሲ ትግበራ ምርጥ ውጤት በማስመዝገብ በፎሬን ፖሊሲ ልዩ ዕትም እውቅና ከተሠጣቸው 10 ዓለም አቀፍ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል ።

ፎሬን ፖሊሲ ልዩ ዕትም በመከላከያናበፀጥታ ዘርፍ  ምርጥ ብሎ የመረጣቸው  ከዓመት ባነሰ  የሥልጣን ዘመናቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ስላደረጉት አስተዋጽኦ ነው ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ በኢትዮጵያበኤርትራ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር በማድረጋቸውም ለረጅም ጊዜ ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል ንግድም ዳግም እንዲጀመር ማስቻላቸውን ጽፏል ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ በኢትዮጵያውያን ከመከፋፈል ይልቅ አንድ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሠጥተው እየሠሩ መሆናቸውንም ጭምር መጽሔቱ አትቷል ።

ጠቅላይ ሚንስትሩም ብዙ ቁጥር ካለው የኦሮሞ ህዝብ በመውጣታቸውም ለወደፊቱ ይሳካላቸዋል ተብሎም እንደሚጠበቅ  መፅሔቱ ጠቁሟል ።