ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተከሰከሰ

ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተከሰከሰ፡፡

በዚህ የመከስከስ አደጋ የሰው ህይወት ማለፉም ነው የተነገረው፡፡

የአደጋውን መንስዔና የተጓዦችን ብዛት ያልጠቀሰው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሁሉ በመንግስትና በኢትዮጵ ህዝብ ስም መፅናናት ተመኝቷል፡፡

አውሮፕላኑ ቢሾፍቱ አካባቢ የተከሰከሰ ሲሆን፥ የነብስ አድን ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል።

እስካሁን ከአደጋው በህይወት ስለተረፈም ሆነ ስለ ሞተ ሰው መረጃ እንደሌለም አስታውቋል።