በአዲስ አበበ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ትላንት በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገለፀ

በአዲስ አበበ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ትላንት ለደረሰው አደጋ የሀዘኑ ተጋሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢምባሲው የአገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ አድርጎ በማውለብለብ በአደጋው የተሰማዉን ሀዘን አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

በአደጋው 8 ዜጓቿን ያጣችው አሜሪካም አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲዋ አማካኝነት የሀዘኑ ተጋሪ መሆኗን ሰንደቅ ዓለማ ዝቅ አድርጋ በማውብለብ ነው የገለጸችው፡፡

ትላንት በኢትዮጵያ በደረሰው የአውሮፕን አዳጋ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ብሄራዊ የሀዘን ቀን ታውጇል፡፡ (ምንጭ፡-የአሜሪካ ኢምባሲ)