የገቢዎች ሚኒስቴር ከ17 ሚሊየን ብር ለታራሚዎች ድጋፍ አደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን 17 ሚሊየን 220 ሺህ ብር የሚገመት አልባሳት ለታራሚዎች ድጋፍ አደረጉ።

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በደቡብ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ሀዋሳ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህግ ታራሚዎች አልባሳቱን በትናንትናው ዕለት አበርክቷል።

የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ሁሉም ዜጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ህገ ወጥነትን ማስቆም ይገባል።

“ህገ ወጥነትን ማስቆም የሚቻለው ደግሞ ከፀጥታ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ርብርብ በማድረግ ነው” ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በያዝነው ሳምንት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ለጌዴኦ ተፈናቃዮች 21 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ ዘይት፣ ስኳርና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።    (ምንጭ ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ)