የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከ25.5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቁሳቁሶች ለጌዲኦ ተፈናቃዮች ለገሱ

ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከ25 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የእርዳታ ቁሳቁሶች የተሰበሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከ56 በላይ መኪናዎች ተጭነው ወደ ጌድኦ መጓጓዙን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የእርዳታ ቁሳቁሱ በከተማዋ ሁሉም ክፈለ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች የወገኖቻችን ችግር የኛም ችግር ነው በማለት የለገሱት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በቦታው ስለ እርዳታ አሰባሰቡ ሁኔታ መግለጫ የሰጡት የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል ወይዘሮ ዓለምፀሀይ ጳውሎስ የአዲስ አበባ ህዝብ ወገኖቹን ለመደገፍ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ድጋፍ የማሰባሰብ ተግባሩ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ወይዘሮ ዓለምፀሀይ ጠቁመዋል።

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጌዴኦ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ30 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡