ዓለም ዓቀፍ የውሃ ቀን ተከበረ

ዓለም ዓቀፍ የውሃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር  ነጋሽ ወጋሹ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት ይህ ቀን ሲከበር የንጽህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት በማቀድ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ላይ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በ6 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚከናወን የ2ኛ ዙር የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ንጽህና መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል፡፡

ዓለም አቀፉ የውሃ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ27ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን÷ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ26ኛ ጊዜ “የንጹህ መጠጥ ውሃና ንጽህና አገልግሎት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡