የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ባንኩ ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘውን ከየክልሎቹ የተፈናቀሉ ዜጎችን ቁጥር መሰረት በማድረግ ለተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የገንዘብ ድጋፉ ክፍፍል መካሄዱን አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት ለሶማሌ ክልል 35 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር፣ ለኦሮሚያ ክልል 33 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር፣ ለደቡብ ክልል 18 ሚሊየን ብር፣ ለአማራ ክልል 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር፣ ለትግራይ ክልል 3 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር፣ ለቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣ ለጋምቤላ ክልል 454 ሺህ ብር፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 387 ሺህ ብር እና ለሀረሬ ክልል 62 ሺህ ብር ነው ድጋፍ ያደረገው። (ኤፍቢሲ)