ከለገዳዲ ግድብ ወደ አዲስ አበባ ያለው የውሃ መስመር ድንገተኛ የመሰበር አደጋ እንደገጠመው ተገለፀ

ከለገዳዲ ግድብ ወደ አዲስ አበባ ውሃ ከሚያስተላልፉ ሁለት የውሃ መስመሮች በአንዱ ላይ ድንገተኛ የመሰበር አደጋ እንደገጠመው የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ለዋልታ የላከው መረጃ እንደሚያመለክተው ከግድቡ ወደ አዲስ አበባ ውሃ ከሚያስተላልፉ ሁለት መስመሮች ውስጥ ባለ9 መቶ ሚ.ሜ. የውሃ ማስተላለፊያ መስመሩ ድንገተኛ የመሰበር አደጋ የደረሰበት ትላንት ምሽት ነው፡፡

የከተማው የውሃና ፍስሽ ባለስልጣን ሰራተኞች በውሃ መስመሩ ላይ የተፈጠረውን የመሰበር አደጋ ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ርብርብ በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ለጥገና ሲባል ውሃ የማስተላለፍ ሂደቱ መቋረጡንና እስከ ፊታችን ማክሰኞ በተወሰኑ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች ውሃ በሙሉና በከፊል እንደማይኖር ባለስልጣኑ አስተውቋል፡፡

አያት አካካባቢ ሰሚት፣ መገናኛ፣ ኮተቤ፣ 22 ካዛንቺስ፣ ኡራኤል፣ ቦሌ ሚካኤልና አየር መንገድ አካባቢ እስከ ማክሰኞ ውሃ የማይደርሳቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ጥቁር አንበሳና ተክለሐይማኖት አካባቢዎች ደግሞ ውሃ በከፊል የሚቋረጥባቸው መሆናቸውን  ተውቋል፡፡

ጥገናውን ጨርሶ ወደ መደበኛ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እያደረገ መሆኑንና እስከዚያው ድረስ ተጠቃሚው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡