የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህጻናት ማቆያ ማዕከል ገነባ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህጻናት ማቆያ ማዕከል ገንብቶ ማስመረቁን ገለጸ፡፡

አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2011 አንቀጽ 48 ማንኛውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለሰራተኞቹ የህጻናት ማቆያ ማዕከላትን እንዲገነባ ይደነግጋል፡፡

በዚህም መሰረት ነው ሚኒስቴሩ ማዕከሉን ያስገነባው፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበራሽ ገብረእግዚአብሄር እንደገለጹት ማዕከሉ ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት ለሚደርሱ ህጻናት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የውስጥ ቁሳቁስ የተሟለለት ሲሆን የጤና ባለሙያዎችና ሞግዚቶችም ተቀጥረዋል፡፡

በአንድ ጊዜ 20 ህጻናትን ማቆየት የሚችለው ይህ ማዕከል የሰራተኞችን ጫና በእጅጉ እንደሚቀንስም ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

የማዕከሉ መገንባት ትልቅ እገዛ እንዳለውም የተቋሙ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡