የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ6 ወራት አፈፃፀሙን ገመገመ

የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራትንና የተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ጥልቅ ግምገማ ማድረጉን አስታወቀ፡፡    

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም እንደገለፁት ተቋሙ የትምህርትና ስልጠና ተደራሽነት፣ ፍትሃዊ፣ ምርማርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማህበረሰቡ አገልግሎት ላይ ትኩረት ተጥቶ እየሰራ ነዉ፡፡ 

በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቃትና የሥራ ተነሳሽነት ያላቸዉ አመራሮች ቦርዱ እንዲመሩ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም የዩኒቨርቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና አባላት የጾታና የብሔር ተዋጽኦን ባማከለ መልኩ የምደባ ስራ ተከናውኗል፡፡

ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል የተማሪዎችና የመምህራን አቅም ምን ደረጃ የገመገመ ሲሆን፣ በሁለቱም በኩል የእንግሊዘኛ ቋንቋ እጥረት እንዳለ ተመልከቷል፡፡

ችግሩን ለመፍታት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች መሰረታዊ እውቀት እንዲኖራቸዉ ለአንድ አመት ያህል ተጨማሪ የመማር ማስተማር ስራ ለማከናወን የወጣው መመሪያ በመገምገም ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡  የመምህራን እዉቀት ለማዳበር ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስልጠና ማዕከል መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡