ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ ወደ ጂማ በመብረር ላይ የነበረ ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ

ንብረትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ ወደ ጂማ በመብረር ላይ ሳለ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ መከስከሱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለዋልታ ቴሌቭዥን ገለጿል፡፡

የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ሄሊኮፕተሩ አምስት መንገዶኞችን ይዞ ሲበር እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ሄሊኮፕተሩ ሊከሰከስ የቻለው በቴክኒክ ችግር ምክንያት ሲሆን በመኖሪያ ቤት ላይ መውደቁም ታውቋል፡፡

የእሳት ቃጠሎ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም በአካባቢው ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋለ አቶ ጄይላን ገልጸዋል፡፡

በዚህ አደጋ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡