ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቻይና ቀዳማዊት እመቤት ፔንግ ሊዩዋን ባዘጋጁት ጉብኝት ላይ ተሳተፉ

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቻይና ቀዳማዊት እመቤት ፔንግ ሊዩዋን ባዘጋጁት ጉብኝት ላይ ተሳትፈዋል።

ለቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ በቻይና ቤጂንግ የተገኙት የሃገራት ቀዳማዊ እመቤቶች በተዘጋጀው መድረክ የቻይናዋ ቀዳማዊት እመቤት ሃገራቸው የሚካሄዱ የልማት ስራዎች ሴቶችንና ህጻናትን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲሆን ትሰራለች ብለዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሣይንስ እና የባህል ተቃም ዩኔስኮ የሴቶችና ታዳጊ ወጣቶች ትምህርት ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ቀዳማዊት እመቤት ፔንግ በሃገራቸው መንግስት በኩል እየተተገበረ የሚገኘው የቤልት ኤንድ ሮድ ማእቀፍ ከሚያከናውናቸው የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችም ባለፈ በህዝብ ለህዝብ መርሃ ግብሮችና የአቅም ግንባታ ስራዎች ሴቶችና ወጣቶችን ባማከለ መልኩ ይሠራል ብለዋል።

በቻይና መንግስት ድጋፍ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ተቋም/ዩኔስኮ/ በቻይና መንግስት በሚደረገው ድጋፍ ቀጣይነት ላላቸው የልማት ግቦች ስኬት የሴቶችና ወጣቶች አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል። ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ