የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ዘላቂ ሰላምና እውነተኛ ፍትሕ እንዲሰፍን እንደሚሰራ ገለጸ

በግጭቶች መሰረታዊ መንስኤዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ዘላቂ ሰላምና እውነተኛ ፍትህ እንዲሰፍን እንደሚሰራ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ኮሚሽኑ በቀጣይ ትኩረት አድርጎ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነተኛና ፍትህን መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈለጊ መሆኑን ኮሚሽኑ አምኖ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል፡፡

የእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ስልጠንና ተግባራት በመነሳት በቀጣይ በግጭቶቹ መንስኤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም ተገልጿል፡፡

የእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ ሰብሰቢ ብርሃን እየሱስ፣ አንተም ተው አንቺም ተው በሚል የማስታረቅ ስልት ሳይሆን በባለሙያዎች የግጭቶችን ምንጭ በማጥናት ይቅር በማባባል በውይይት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ይሰራል ብለዋል፡፡

የሚቀርቡ አቤቱታዎችንም በባለሙያዎች ምርምራ በማድረግ የቅሬታዎችን መንስኤዎች በመመርመር ዘላቂ ሰላምና እውነተኛ ፍትህ እንዲሰፍን ጥረት እንደሚደረግ ከመግለጫው ለመረዳት ተችሏል፡፡