በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ዙሪያ ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

"ሚዲያ በዴሞክራሲ ጋዜጠኝነትና ምርጫ በዘመነ መረጃ ብክለት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ በመገነኛ ብዙኃን ላይ እየገጠሙ ስላሉ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶችን የተመለከቱ የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተዋል፡፡

በፕሬስ ላይ እየታዩ ያሉ ተጽንኦች በመንግስት፣ ሚዲያው በራሱ እና በፓርቲዎች እንደሆነ በውይይቱ ተጠቁመዋል፡፡

በሀገሪቱ ላይ ያለው የግልና የመንግስት መገነኛ ብዙኃን መረጃውን በነፃነት የማግኘት መብታቸው እኩል አለመሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የመገነኛ ብዙኃን በሚያስገቧቸው ዕቃዎች ላይ የሚጣለው ታክስ ሚዲያው እንዳይጠናከር አድርጓልም ነው የተባለው፡፡

በአሁኑ ወቅት በሚዲዎች ላይ የጋዜጠኞች የአቅም ውስንነት፣ ጋዜጠኝነትን ከአክቲቪዝም ጋር አንድ አድርጎ የማየት ሁኔታ መኖርና የሚዲዎች አለመቀናጀት በዘርፉ እንደ ተግዳሮት ይታያልም ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል በሀገሪቱ አሁን እየታየ ያለውን የሚዲያ ነጻነት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባና መገነኛ ብዙኃን በኃላፊነት መስራት እንዳለበት በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡