የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ

የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ ገብቷል።

አስክሬናቸው ከጀርመን ተነስቶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።

በነገው እለትም በሚሊኒየም አዳራሽ አስክሬናቸው የሽኝት ስነ ስርዓት የሚከናወንለት ሲሆን፥ ከሰዓት በኋላም የቀብር ስነ ስርዓታቸው የሚከናወን ይሆናል።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ባለፈው ቅዳሜ ነበር በጀርመን ሀገር ህይወታቸው ያለፈው።