ዛሬ ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ ይውላል

ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ህልፈት አስመልክቶ ያወጀው ብሄራዊ የሀዘን ቀን በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ልዩ ስብሰባው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ የአንድ ቀን ብሄራዊ የሃዘን ማወጁ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረትም ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 28 ቀን 2011 የሪፐብሊኩ ሰንደቅ አላማ በመላው የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች እና በውጭ ሀገር በሚገኙ ኤምባሲዎችና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ዝቅ ብሎ የሚውለበለብ ይሆናል።

የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሚያዝያ 19 2011 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

የቀብር ስነ ስርዓታቸውም በትናንትናው እለት የፌዴራልና የክልል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች በተገኙበት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብራቸው ሲፈፀምም ለክብራቸው ሲባል 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶላቸዋል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በ1935 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን ፥ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በጀርመን ፍራንክፈረት ሚያዚያ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።