ሐጅ ሙሐመድ አሚን ጀማል ኃላፊነታቸውን ለቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ አስረከቡ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሐጅ ሙሐመድ አሚን ጀማል ኃላፊነታቸውን አዲስ ለተቋቋመው የአሊሞች ምክር ቤት ሰብሳቢ ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ አስረከቡ።

በመጅሊሰ ታሪክ የመጀመሪያው ሰላማዊ የሰልጣን ርክክቡ በዛሬው እለት ነው የተካሄደው።

የስልጣን ርክክብ ሂደቱ አዲሱ የኡለማና የባላደራ ቦርድ ኮሚቴዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴዎች በተገኙበት በሰላም መጠናቀቁም ተገልጿል።

የአሊሞች ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 23 2011 ዓ.ም በተካሄደው “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ እና የአንድነት” ሀገር አቀፍ ስብሰባ ላይ ነበር የተመረጠው።

ከ300 በላይ ኡለማዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት በተሳተፉበት ጉባዔ 23 አባላት ያሉት ጊዜያዊ የኡላማዎች፣ ምክር ቤቱን መምረጡም ይታወሳል።