ሀገርን ለማሳድግ ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት መስጠት ይገባል – አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ

ሀገርን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ የትምህርት ዘርፍ ላይ መረባረብና ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ተናገረ፡፡ 

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቆይታ ዋልታ በዋግህምራ ዞን የዳስ ውስጥ ትምህርት ቤቶች አሰመልክቶ የሰራው ዜና ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠረበትና በቅርቡም በስሙ በትምህርት ቤቶች ግንባታ ላይ ያተኮረ ፋውንዴሽን እንደሚያቋቁም ገልጿል፡፡  

ሀገር እንዲያድግና ዜጎች ከድህነት ኢንዲወጣ ለማስቻል ቀዳሚ የሚሆነውን የትምህርት ልማት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ተናግሯል፡፡

በዘርፉ የሚታዩን ችግሮች አመራር ብቻ ሳይሆን ሁሉም አካላት የበኩሉን አሻራ ማሳረፍ እንዳለበት ጠቁሟል፡፡

አትሌቱ በአሁኑ ወቅት ችግሩን ከማጉላት ይልቅ በመፍትሔው መስራት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

አትሌት ሀይሌ በዋግ ኸምራ ብሄረሰብ ዞን በፃግብጂ ወረዳ የሚገኝን አንድ ትምህርት ቤት እስከ መጪው መስከረም 2012 ዓ.ም ሰርቶ ለማስረከብ ዝግጅቶች እያከናወነ እንደሆነ ይታወሳል፡፡