ከረመዳን ኢድ በአል ጋር በተያያዘ የሀገር አቀፍ የፈተና መስጫ ቀን ተራዘመ

የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት ባደረገው ስብሰባ ከኢድ በዓል ጋር በተያያዘ የሀገር አቀፍ የፈተና መስጫ ቀን መራዘሙን አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡ የ10ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 3፣ 4 እና 5፣ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10፣እና 11/2011ዓ.ም. ሲሆን፤ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 12፣13 እና 14/2011 ዓ.ም. ሆኖ  ተቀይሯል።

የፈተና ጊዜ ለአስተዳደራዊ አመቺነት ሲባል የተቀየረ መሆኑን የገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር ኮማንድ ፖስቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከህብረተሰቡ ጥያቄ በተጨማሪም ፈተና ተፈታኞችና ፈታኞች ከበዓሉ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ከቦታ ቦታ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠርና የፈተናውን ሂደት የተሳካ ለማድረግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

(ምንጭ፡-የትምህርት ሚኒስቴር)