ጠ/ሚ ዐቢይ የትራንስፖርት ሚኒስቴርና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትራንስፖርት ሚኒስቴርና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጉብኝት አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትራንስፖርት ሚኒስቴር ተቋማዊ ዕድሳትና የአሰራር ማሻሻያ ላይ ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል።

የተደረገው ማሻሻያ የተቋሙን የተልዕኮ ጥራት ለማስጠበቅ እንደሚያግዝ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጎብኝተዋል።

ሚኒስቴሩ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ሁኔታን በመፍጠር ለሌሎች መስሪያ ቤቶች እንደ ሞዴል ስለሚወሰድ መጎብኘታቸውም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ የሳይንስና ቴክሎጂ ሚኒስቴር የአሁኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ ያሰሯቸውን ስራዎችም ጎብኝተዋል።

የተቋሙን አደረጃጀትና አሰራር ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የተሻለ ስራ ለመስራት  መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡